የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት በሰላም መጣችሁ። ጽሕፈት ቤታችን የወረዳችንን ነዋሪዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችና ጥቅሞች ለማስከበር ወሳኝ የሆኑትን የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎቶችን በቅንነት፣ በታማኝነትና በግልጽነት ለመስጠት ሌት ተቀን እየሠራ ይገኛል። ዋነኛ ዓላማችን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓታችንን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከወረቀት ቢሮክራሲ የጸዳ በማድረግ ለእያንዳንዱ የአካባቢያችን ነዋሪ የሚገባውን ጥራት ያለውና ፈጣን ምላሽ መስጠት ነው።
የአንድ አካባቢ ሁለንተናዊ ልማትና መልካም አስተዳደር የሚረጋገጠው ትክክለኛና ወቅታዊ የነዋሪዎች መረጃ ሲኖር ነው። በመሆኑም ጽሕፈት ቤታችን የሕዝብ መረጃዎችን በአግባቡ በመያዝ፣ የተደራጀና ተዓማኒነት ያለው የመረጃ ሥርዓት በመገንባት የወረዳችንን የልማት ዕቅዶች ስኬታማ ለማድረግ የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የአሠራር ማሻሻያዎችን በመተግበር፣ የአገልግሎት ፈላጊዎችን እንግልት ለመቀነስና እርካታን ለማሳደግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን ቀጥለናል።... ተጨማሪ ያንብቡ
ወ/ሮ ሲዲሴ ባይሳ , የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ


